ተቋማችን የአካቶ ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ በዘርፉ እውን ማድረጉ
ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎቻችን የትምህቱን ሂደት በእጅጉ ያቀለዋል፡፡
ከመደበኛ ስልጠና በተጨማሪ የኮምፒውተር ስልጠና፣ የስነ ልቦናና
የአጠናን ዘዴ ስልጠና በነጻ መስጠታችን፤ በሲሙሌተር ወይም ምስለ ተሸከርካሪ ማሰልጠናችንን ጨምሮ የተሟላ የቤተ ሙከራ እና የቤተ
መጽሃፍት አገልግሎትም እንሰጣለን፡፡
ኪ ባይ ኪ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እየተሳተፈ ብቁ ዜጋን
ከማፍራት አኳያ ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
ከነዚህም መካከል የታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክት በማቋቋም ወጣቶች ጊዜያቸውን
በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማድረግ እንዲሁም ወላጆቻቸውን በትራፊክ አደጋ ላጡና ችግረኛ ለሆኑ ወጣቶች ነጻ የትምህት እድልን ያመቻቸ ለህዝብ
የሚሰራ ተቋም ነው፡፡
ተቋማችን ብቃት ባለው አስተዳደር የሚመራ ሲሆን አሰልጣኞቻችን በአውቶሞቲቭ
የተመረቁ በሙውያው ተቀባይነት ያላቸው እንዲሁም በማስተማር ከ 5 አመታት በላይ ልምድን ያካበቱም ናቸው፡፡
እኛ ዘንድ ሲመጡ በማራኪ ክፍሎቻችን፣ በተደራጀ ቤተ ሙከራ እንዲሁም
ቤተ መጽሃፍት ራስዎን በቁ እንዲያረጉ ይታገዛሉ፡፡ የቴክኒክ ብቃ ያላቸው መኪኖቻችን፣ አቅምን ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ ክፍያችንን
ጨምሮ በማራኪ አቀባበላችን ተደስተውና ሰልጥነው ብቁ ሆነው ይመረቃሉ፡፡